የኢትዮዽያ ስፖርት አካዳሚ ለአዲስ አበባና ለአሰላ (አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል) የ2015 ዓ.ም የዕጩ ሰልጣጮች ምልመላ አካሄደ።

ነሀሴ 25/2014 ዓ.ም
 
የኢትዮዽያ ስፖርት አካዳሚ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ከመንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት ለአዲስ አበባና ለአሰላ (ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል) ካምፓሶች በ2015 ዓ.ም አካዳሚውን ለአራት አመት ስልጠና የሚቀላቀሉ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 54 ወንድ እና 97 ሴት በድምሩ 151 ሰልጣኞችን ለአዲስ አበባው ካምፓስ 41 ወንድ እና 68 ሴት በድምሩ 109 ሰልጣኞችን ለአሰላ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ በአጠቃላይ ለሁለቱም ካምፓሶች 95 ወንድ እና 165 ሴት በድምሩ #260 እጩ ሰልጣኞችን እድሚያቸው ከ17 አመት በታች የሆኑ ችሎታው ወይም ተሰጥኦው ያላቸውን ታዳጊ ስፖርተኞችን በእግርኳስ፣ በቮሊቦል፣ በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በወርልድ ቴኳንዶ፣ በፓራ_አትሌቲክስ፣ በቦክስ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በአትሌቲክስ እና በብስክሌት ስፖርቶች የመጀመሪያ ዙር በርካታ እጩ ሰልጣኞችን ሲመለምል ቆይቷል። 
ምልመላው የተሳካ እንዲሆን አካዳሚውን በተለያየ መንገድ ትብብር ያደረጋችሁልን ባለድርሻ አካላት ለሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮዎች፣የስፖርት ባለሙያዎች፣የፕሮጀክት አሰልጣኞች፣ዞኖች፣ወረዳዎች፣የሚዲያ አካላት እና ሌሎችም ያልጠቀስናችሁ አካላት ለመልማይ ቡድኑ ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ እና እጩ ተመልማዮችን ደረጃውን በጠበቀ ማዘውተሪያ ስፍራ እንዲመዘኑ አመራር በመስጠት ለተባበራችሁን በሙሉ #የኢትዮጵያ_ስፖርት_አካዳሚ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።
በመጨረሻም በምልመላው አካዳሚው ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የመለመላቸውን እጩ ሰልጣኞችን ወደ አንድ የመረጃ ቋት በማስገባት የተሻለ ውጤት ያላቸውን እጩ ሰልጣኞች በመለየት በቅርቡ በአዲስ አበባ የመጨረሻ ዙር ምልመላ ስለሚኖር በሰጣችሁን ስልክ የምንደውል ስለሆነ ስልካችሁን ክፍት እንድታደርጉ በተጨማሪም በአካዳሚው የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ-ገፅ የምናሳውቅ መሆኑን እየገለፅን በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን።

ነሀሴ 25/2014ዓ.ም

Leave a Reply