ማዕከሉ በ52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ6ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ።

ግንቦት 13/2015 ዓ.ም

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየውና የተለያዩ ክለቦች፣ ክልሎች፣ከተማ መስተዳድሮች እና የስፖርት ተቋማቶች የተሳተፉበት 52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ፍፃሜውን አገኘ።

በሻምፒዮናው ማዕከሉ ዛሬ ከተሳተፈባቸው የፍፃሜ ውድድሮች በከፍታ ዝላይ ሴት ኛጆክ ፖል 3ኛ ደረጃን በመያዝ የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ስትሆን በ5000 ሜ ወንድ፣ በ4×100 ሪሌ እና 4×400 ሜ ሪሌ ወንድ/ሴት የዲፕሎማ ተሸላሚ ሆነዋል።

በ52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በመዝጊያ ውድድሮች በሴቶችና በወንዶች አሸናፊ ቡድኖች የዋንጫና የገንዘብ ሽልማት ከአምባሳደር መስፍን ቸርነት ተቀብለዋል።

ማዕከሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ መቻል ክለብን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን፣ኦሮሚያ ክልልንና ሲዳማ ክለብን ተከትሎ በሴት 55 ነጥብ በመያዝ 3ኛ ደረጃ ሲይዝ በወንዶች 68 ነጥብ በመያዝ 6ኛደረጃ በድምሩ 123 ነጥብ በአጠቃላይ በሻምፒዮናው የ6ኛ ደረጃ በመያዝ 52ኛውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በድል አጠናቀዋል።

በመጨረሻም የማዕከሉ ሁሉም አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የማዕከሉ ሰራተኞች በተመዘገበው ውጤት #የእንኳን_ደስ_አላችሁ!! መልዕክት ማዕከሉ አስተላልፏል።

Leave a Reply