በማዕከሉ ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪ ቃል የማዕከሉ አመራሮች፣ሰራተኞች እና አሰልጣኞች የችግኝ ተከላ አሻራቸውን አሳረፉ።

በማዕከሉ ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪ ቃል የማዕከሉ አመራሮች፣ሰራተኞች እና አሰልጣኞች የችግኝ ተከላ አሻራቸውን አሳረፉ።

*********🌿🌱🌱🌿☘️🍀🌲*

ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ሀገራችን ኢትዮጵያ ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በተነሳችበት መርሃ ግብር ላይ የማዕከሉ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና አሰልጣኞች አሻራቸውን አሳርፈዋል።

ዛሬ ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ጀምሮ በማዕከሉ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩን የማዕከሉ ዲን አቶ ጎሳ ሞላ ያስጀመሩ ሲሆን በእለቱ ለችግኝ ተከላ በተዘጋጀበት ቦታ ላይ የተለያየ ዝርያ ያላቸው በርከት ያሉ ችግኞችን ሁሉም የማዕከሉ ሰራተኞች ችግኝ ተከላውን አከናውነውል።

Leave a Reply